Addis Zemen (Sep 25, 2026)
ግስፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/BGR/002/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን የተቃጠሉ ትራንስፎርመሮችን ባሉበት ሁኔታ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
|
1 |
የተቃጠሉ ትራንስፎርመሮች |
ሪጅን ስቶር |
በቁጥር |
17 በላይ |
50,000.00 |
ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 |
ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር (1000153727906 ) EEU Benishangul Gumuz Region) የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ/ ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ፅ/ቤት ሰፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 105 በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ፅ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 208 ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት።
8. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 057 275 4844 / 0917 703 634 / 0917 834 762 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ፅ/ቤት