የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል አቅርቦቶችን በየወሩ ለሚያቀርቡ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል አቅርቦቶችን በየወሩ ለሚያቀርቡ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ወማተ/አ2/470/2019

የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ3 ወራት በሚቆይ የአቅርቦት ጊዜ ሆኖ በአቅራቢና ተቀባይ መካከል በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት ሶስት ወራት ለሚደርስ የግዥ ዘዴ በየወሩ ለሚያቀርቡ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል።

 ስለሆነም ፡-

ተ.ቁ

 

የአቅርቦቱ አይነት

 

መለኪያ

 

የአቅርቦት መጠን

የማቅረቢያ ጊዜ

 

ርክክቡ የሚፈፀምበት ቦታ

በቅድሚያ ለ03 ወራት ቆይታ ጊዜ ከ——እስከ

01

ነጭ ሠርገኛ ጤፍ

በኩ/ል

ከ150-200 ኩንታል

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

02

ነጭ በቆሎ

 

በኩ/ል

ከ450-650 ኩንታል

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

03

ባቄላ

 

በኩ/ል

ከ60-80 ኩንታል

 

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

04

የሀገር ውስጥ ስንዴ

በኩ/ል

ከ40-45 ኩንታል

 

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

05

የሽሮ ጓያ

 

በኩ/ል

ከ40-50 ኩንታል

 

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

06

ጎመን ዘር

 

በኪ.ግ

 

ከ20-50 ኪ.ግራም

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

07

ቀይ ሽንኩርት ቀላፎ

በኪ.ግ

 

ከ500-600 ኪ.ግራም

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

08

የዳቦ እርሾ

 

በፓኬት

 

ከ30-40 ፓኬት

 

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

09

ሻይ ቅጠል

 

በፓኬት

 

ከ100-180 ፓኬት

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

10

ጨው

በኩ/ል

ከ5-6 ኩንታል

 

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

11

የተፈጨ በርበሬ 1ኛው

በኪ.ግ

 

ከ150-280 ኪ.ግራም

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

12

ግንዲላ የማገዶ እንጨት

በሜ ኩ

ከ50-80 ሜትር ኩብ

ወር በገባ ከ25-30ድረስ

ተቋሙ ቅጥር ግቢ

ከ 1/02/2019-30/04/2019

መመዘኛዎች፣

(01) በየመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ላት/፤ የዘመኑን ግብር የከፈለች፤የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ላት/፤ ከማንኛውም ግብርና ታክስ ከፋይነት ነፃ እንዲሆኑ ከተፈቀደላቸው ድርጅቶችና ዩኒየኖችና ተመሳሳይ የንግድ ድርጅቶች በስተቀር የVAT 15% ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸው፤

(02) ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አቅርቦት በቀደምት የሥራ ዘመን ተጫርተው በማሸነፍ ለማረሚያ ተቋማት ወይንም ለሌሎች መንግስታዊና ሕዝባዊ ድርጅቶች ለ01 (አንድ) አመት እና ከዚያም በላይ ለሆነ ጊዜያት ያለ እንከን ስለማቅረባቸው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ደብዳቤ |ምስክር ወረቀት/ ማስረጃ ከሌሎች መጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ፤

(03) አሸናፊው ተጫራች ለአቅርቦቱ ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሠረት ከጥቅምት 1/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ወራቶች በየወሩ ለማቅረብ ህጋዊ የውል ሰነድ የሚፈርምና ያሸነፈው ነጠላ ዋጋ እንደተጠበቀ ሆኖ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሚሆን ፣

(04) ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመንጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/ደ/ሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን፤ የጨረታ ማስከበሪያን በሚመለከት ከጠቅላላ አቅርቦት ዋጋ 2% የብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ CPO/ተመሳሳይ ሰነድ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

(05) ተጫራቾች፡- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት የእያንዳንዱን እህል ማጣፈጫ የአንዱን ኩንታል/ኪ/ግራም/ ነጠላ ዋጋ ከነማስረጃው ኮፒዎች ጋር በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አዘጋጅተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

(06) ተጫራቾች የእህል ዓይነቶችን እና የበርበሬ ናሙና የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም

(07) ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ህጋዊ/ወኪሎቻቸው በተገኙበት 11ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት በማረሚያ ተቋሙ ቅጥር ግቢ አዳራሽ /ቢሮ/ የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ ዕለቱ የበዓላት /የዕረፍት/ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እያሳሰብን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 011-330- 0154 ፣ 011 -330 1139 ፣ 011- 330–158
የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *