በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የአፄ ናኦድ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ግዥ የሚያስፈልገውን የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የአፄ ናኦድ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ግዥ የሚያስፈልገውን የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 29, 2026)

ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2019

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የአፄ ናኦድ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ግዥ የሚያስፈልገውን የተለያዩ

  • ሎት 01 አላቂ የትምህርት እቃዎች
  • ሎት 02 አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 03 የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 04 የደንብ ልብስ
  • ሎት 05 የቋሚ እቃዎች
  • ሎት 06 ልዩ ልዩ የስፖርት እቃዎች
  • ሎት 07 የህንፃና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 08 ልዩ ልዩ የሕትመት ስራዎች
  • ሎት 09 የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት 10 የልዩ ልዩ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ዕቃዎች የእጅ ዋጋ
  • ሎት 11 የተለያዩ አገልግሎት የሚውል ቆሎ እና ውሃ
  • ሎት 12 የተለያዩ የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት ክፍያ

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅደሚያ በማሟላት የጨረታ ሰነዱን የአፄ ናኦድ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት እየመጡ መውሰድ ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። በመንግስት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል Tin No. ያላቸውና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የጨረታውን ሰነድ በነፃ ይወስዳሉ ከአደራጃቸው ተቋም ወቅታዊ የሆነ በአድራሻችን የተፃፈ የአምራችነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያና ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ብር 20,000/ ሃያ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የአፄ ናኦድ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአፄ ናኦድ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።

7. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ ተሞልቶ ኦርጅናሉና ኮፒው ተለይቶ በፖስታው ላይ ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ያልቀረበበት እና የዘገየ በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ እንዲሁም ከጨረታ ሠነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

9. ተጫራቾች 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

10. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚቀርብበት ምርት /እቃ ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ምርት/ እቃ ከገበያ ላይ ገዝተው ለሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

11. መ/ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡– አምስት ኪሎ ወደ ቅድስተ ማሪያም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር፡– 011 154 2338

የአፄ ናኦድ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን