Addis Zemen (Sep 29, 2026)
የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች
ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ – የም/ዘ/አ/ዘ/ግጨ/ሸ01/2019
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት(ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
2. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
3. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። የዕጣን ምርቶች ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል።
4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሀሙስ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-5፡30፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊትለፊት በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 እንዲሁም በአዳማ ከተማ መብራት ኃይል ንግድ ምክር ቤት ጎን አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ጨረታው ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት በምርጥ ዘር አቅርቦት በዘርፉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110ና በኮርፖሬሽኑ አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ምርቶች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይቻላል።
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
8. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
አዲስ አበባ 011 470-8475 / 011 666-2390
አዳማ 022 111-2122 / 022 111-3156
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ