የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ለቡና መቁላት፣ መፍጨትና ማሸግ ስራ የሚያገለግሉና ጣሊያን ስሪት የሆኑ ማሸነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ለቡና መቁላት፣ መፍጨትና ማሸግ ስራ የሚያገለግሉና ጣሊያን ስሪት የሆኑ ማሸነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 22, 2026)

የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት የተገለጹትን ከአቶ ብሩህ ተስፋ ጥሩነህ ባልተከፈለ ዕዳ ምከንያት   በአዋጅ ቁጥር103/1990 እና 807/2005 መረከባቸውንና ከዚህ በታች በዝርዝር ለቡና መቁላት፣ መፍጨትና ማሸግ ስራ የሚያገለግሉና ጣሊያን ስሪት የሆኑ ማሸነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታለመሸጥ ለማከራየት ይፈልጋል።

ተ.ቁ.

የንብረቱ ዝርዝር

ብዛት በቁጥር

የሐራጁ መነሻ ዋጋ

የንብረቱ ሁኔታ

ሐረጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

Coffee Roasting and Grinding Machinery

 

     

1.1

Pneumatic Loader Model ELP60

1

 

 

 

84,205,883.24

 

 

 

 አዲስ

 

 

 

 

ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

1.2

Coffee Roaster Model – TTG 60

1

1.3

Roasted Coffee Receiving Hopper

1

1.4

Loader (Pneumatic Conveyor system

1

1.5

Suction Pump group for Pneumatic conveyor system

1

1.6

Silos for roasted coffee beans

2

1.7

Drop diverter valve

2

1.8

Additional Unit of Pneumatic conveyor to feed the roasted coffee beans to packing machine

1

1.9

Coffee Grinder Model-MAIN 300

1

1.10

Raking Screw Conveyor to feed the ground coffee to silo

1

1.11

Ground Coffee Silo

1

1.12

Electric Control Panel Molim

1

2.

Auto Weighing and Vertical Packaging Machinery Brand: DOLZAN, Model: D150-C1, Origin: Italy, Manufacturing Year: 2021

1

 
የዝግ ጨረታው መመሪያ፡
  1. በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻውን እንዲሁም ንብረቱን የሚገዛበትን ዋጋ የሚገልጽ ማመልከቻ ፣የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፣የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር16,841,176.65/ አስራ ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አንድ ሺ አንድ መቶ ሰባ ስድስት ብር ከ65/100 ሳንቲም/ የያዘ በኢ/ት ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪከት ስም የተዘጋጀና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አያይዞ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢ/ት ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪከት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላል።
  2. ንብረቱ በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ይርጋለም ከተማ፣ ይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቪድ ውስጥ ይገኛል።
  3. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል። ፈቃዱን ካላገኘ ግን የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል።
  4. ንብረቶቹን ሙሉ በሙሉ በካሽ/ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የታክስ ክፍያዎችን ጨምሮ ይከፍላል፡።
  5. የጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። የጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው በድጋሚ ይካሄዳል። ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ወዲያወኑ ይመለስላቸዋል።
  6. ተጫራቹ በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ ባንኩ ማሸነፉን እንዲያውቅ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ቀሪ ክፍያ አጠቃሎ በመክፈል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  7. የካፒታል ዕቃውን ካለበት ይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሺድ ወደ ሚፈልግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣የመትከያ፣ስራ የማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ዥው ተከራይ ይሸፍናል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ይካሄዳል።
  9. ስለ ንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ዎርክአውት ዲቭዥን በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
  10. ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ዎርክአውት ዲቭዥን ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።
  11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት
 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *