Addis Zemen (Oct 24, 2026)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-001/2019
በቤ/ጉ/መንግስት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ በከተማ አስተዳደሩ ስር ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች እና ለጥጉ ሠራተኞች አገልግሎት የሚውል
- የደንብ ልብስ፣
- የስፖርት መምህራን ልብስ፣
- ኤሌክትሮኒክስ፣
- የመንገድ ዳር መብራት ዕቃዎች
- ሞተር ሳይክሎች፣
በመደበኛ በጀት ግዥ መፈረም ይፈልጋል።
- ሎት 1፡ – የደንብ ልብስ
- ሎት 2፣ የመምህራን የስፖርት ልብስ
- ሎት 3፡ ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 4- የመንገድ ዳር የመብራት ዕቃዎች
- ሎት 5፡–ሞተር ሳይክል እና ባለ3 እግር ባጃጅ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ።
1ኛ/ ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የስራ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2ኛ/ ተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል
3ኛ/ ተጫራቾች የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ያላቸው።
4ኛ/ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርትፈኪት(ቲን ነበር)።
5ኛ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ CPO/ በእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000 /አምሳ ሺህ/ ብር ማስያዝና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡የማንኛውንም የባንክ ቢድ ቦንድ የማንቀበል መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን።
6ኛ/ተጫራቾች የእቃውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ በአድስ አበባ መ/ቤታችን በሚያመቻቸው ቦታ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 400 /አራት መቶ ብር / ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
7ኛ/ ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ሞልተው በየሎቱ አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ፣ ሁለት የቴክኒካል ኮፒ ዶክመንት አና አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል ዶከመንት እና ሁለት ፋይናንሻል ኮፒ ዶክመንት ለያንዳዳቸው በተለያየ ፖስታ በማድረግ በአንድ ማዘር ፖስታ በታሸገ ኢንቨሎፕ ታሽጎ ሰነዱን በገዘበት ከፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ አለባቸው።
8ኛ/ ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9ኛ/ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
10ኛ/ አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በነጠላ ዋጋ ሆኖ የተሻለ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበና የተሸለ ናሙና የቀረቡ መሆናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
11/ መምሪያው የተሻለ ዘዴና አማራጭ ካገኘ ጨሪታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
12/ ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዕቃ አስፔስፊኬሽኑን ከተያየዘው ውጭ ናሙና ማቅረብይጠበቅባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ፡–
በስልክ ቁጥር 0909449652 /0917181578 /0917426395 /09108508456 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ።
በቤ/ጉ/ክ/መ/የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ