Melekite Dire (Oct 21, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ድዳ አሁ/ደ/ት/ቤት ግ/ጨ/01/2019
የድሬዳዋ ጎሮና ቡቱጅ 1ኛ ና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ለትምህርት ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሣርያዎች፤ የፅዳት እቃዎች እና ኮምፒትር እቃዎችና ጥገናዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊና ብቃት ያላቸውን የሀገር ውስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል።
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ታሽጎ ከጠዋት 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎሮና ቡቱጅ 1ኛ ና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራሂደት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራጮች በጨረታ ሰነድ አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነድ የሚከተሉት ናቸው፡፡ በዘርፍ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውና በዘመኑ ስለመታደሱ የተረጋገጠ፤ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ በአቅራቢነት የተመዘገበ፤ በተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ከዚህ በታች በተገለፀው ሰንጠረዥ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ባንክ ጋራንቲና ሲፒኦ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በባንክ የተረጋገጠ ባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ባንክ ጋራንቲና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሲፒኦ/ጥሬ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ባንክ ጋራንቲና ሲፒኦ(CPO) ያልያስያዘ ቢኖር ሰነዱን ብቻ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ዋጋ የለውም።
|
ሎት |
የዕቃዎች መገለጫ |
የጨረታ ማስከበርያ |
|
ሎት አንድ Lot One |
አላቂ የቢሮ እቃዎች እና አላቂ የትምህርት እቃዎች |
5000.00 |
|
ሎት ሁለት Lot Two |
አላቂ የእስፖርት እቃዎች |
5000.00 |
|
ሎት ሶስት(LOT)three |
የፅዳት እቃዎች |
5000.00 |
|
ሎት አራት (LOT) four |
የኮምፒትር እቃዎች |
5000.00 |
|
ሎት አራት (LOT) five |
የኮምፒትር ና ኤሌክተሮኒክስ ጥገና |
5000.00 |
|
ሎት አራት (LOT) six |
የንብረት ጥገና |
5000.00 |
2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃዎች ናሙና የጨረታ ሰነድ ጋር በጨረታው መክፈቻ አለት ማቅረብ አለባቸው
3. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዥ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ባንከ ጋራንቲና ሲፒኦ(CPO) በቅድሚያ ማስያዝ በተጨማሪም ተጫራቾች አቅርቦቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አግዘው በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡የእቃ ሳምፕል ማቅረብና ከተጠየቀው የእቃ መግለጫ (specification) ወጪ ቢቀርብ ተቀባይነት የለውም።
4. ትምህርት ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
5.ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራርያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮና በቱጅ 1ኛ ና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ድሬዳዋ
ስልክ ቁጥር 0966 277 968/0981 274 757