የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ ለስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ ለስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 29, 2026)

የግልፅ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ ለስፔርፓርት የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች በ24/02/2019 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቀ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፦

1. ግልፅ እና ለሀራጅ ጨረታ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤

2, ለሐራጅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማቅረብ የሚችል፤

3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤

4. ለሐራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ ለራሱ ያቀርባል፤

5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤

6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆነ አለበት፤

7. እቃዎቹን አሽንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤

8. በጨረታው ያሳሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤

9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤

10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ዕርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤

11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሽኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤

12. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ በ24/02/2019 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቀ/ጽ/ ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ26/02/2019 3፡45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤

13. የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው በ26/02/2019 ከረፋዱ 4:15 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

N.B – አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ ቤት