Addis Zemen (Oct 29, 2026)
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ኦላይን የግልጽ ጨረታ ቁጥር AE02/2019
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወታየው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ ኦላይን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በግልጽ ጨረታ ቁጥር AE02/2019 በ27/02/2019
- የተለያዩ ሞባይል ቀፎዎች፤
- እስፔርፓርት፣
- ጫማ፤
- የግንባታ እቃ፤
- ቴሊቪዥን እና የተለያዩ ዕቃዎች ባሉበት በአላይን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች
- በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሠጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
- በግልጽ ጨረታው ላይ በመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት 100 ብር በመከፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ አላይን መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ አና የዕቃዎቹን ሳንፕል ማግኘት ይችላሉ። እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ጨረታው የሚካሄደው ሙሉ ለሙሉ በኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ነው።
- በግልጽ ጨረታ በሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
- በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ የሰጡት ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs COMMSSON DREDAWA BRANCH OFECE) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ በአካል ወደ አክሸን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕሳትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ግልጽ ጨረታ ኦላይን ከሆነበት ከ20/02/2019 4:00 ጀምሮ እስከ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 27/02/2019 4:00 መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ይሆናል።
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 9 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች በጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- የጉምሩከ ኮምሸን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን በማግኘት በስልክ መስመር 05-11-5511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 (09 12 88 57 46) መደወል ይቻላል
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት