Reporter (Nov 01, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር በቃሊቲ መጋዘን የሚገኙትን የተለያዩ ሸቀጦችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የዚህን ጨረታ ሰነድ በተገለፀው አድራሻ በመግዛት ማንኛውም ተወዳድሮ ያሸነፈው አካል እቃዎቹን መግዛት የሚችል ሲሆን:-
- የጨረታ አይነት፡– የውሃ ፓምፕና መለዋወጫ፣ ጄነሬተርና መለዋወጫዎች፣ የተለያዩ ትራክተሮች መለዋወጫዎች በተለዩት የጨረታ ሰነዶች በጥቅል (በሎት/ LOT) አደራጅቶ ገዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ነው፤
- ማንኛውም ተጫራች (የተፈጥሮም ይሁን ሕጋዊ ሰውነት ያለው) በአንድ የጨረታ ሎት /Lot/አይነት ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ገዝቶና ሞልቶ ማስገባት አይችልም። ሆኖም ሻጭ ለሽያጭ ባወጣቸው የተለያዩ ሎቶች ላይ በሁሉም ላይ በመሳተፍ ዋጋ ማቅረብ ይችላል። እያንዳንዱ ተጫራች በተመሳሳይ ሎት (በአንድ ሎት) ላይ ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ሞልቶ ማቅረቡ ከተረጋገጠ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
- ሻጭ ይህንን ጨረታ ሰነድ በመሸጡ ምክንያት በማንኛውም ሁኔታ የውል ስምምነት እንዲፈጽም አያስገድደውም። የውል ስምምነት እንደያዘም አይቆጠርም።
- ተጫራቾች ለመግዛት ዋጋ የሰጡበትን የንብረት/ሸቀጥ አይነት ወይም የሎት አይነት ጠቅላላ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ዋጋ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በኩባንያው ዋና መ/ቤት ወይም በሁሉም ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ላይ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሎቶች /Lots/ በመግዛት መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የሻጭ አድራሻ ማለትም አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ከሚገኘው አምባሰል ህንጻ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 503 ;አዲስ አበባ ፣በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ ዜጋ ለመሆናቸው ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም ፓስ ፖርት ኮፒ እንዲሁም የንግድ ድርጅቶች ከሆኑ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከታወጀበት እለት 22/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ማለትም በ09/03/2019 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ይታሸጋል። የኩባንያው ንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ከየቅርንጫፉ የጨረታ ሰነዶች የሚመጡበትን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ማለትም በ14/03/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሻጭ አድራሻ ማለትም አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ከሚገኘው አምባሰል ህንጻ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 305 የጨረታ ሰነድ የመከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በጨረታ ሰነድ የመከፈት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን ዋጋ አያሳጣውም።
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ለሚያወጡት የትኛውም ዓይነት ወጭ (በጨረታው ተሳትፎ ቢያሸንፍ፣ ቢሸነፍ፣ በተለያየ ምክንያት ከጨረታው ውጭ ቢደረግ ወይም ጨረታው ቢሰረዝ) ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም።
- በጨረታ ሰነዶቹ ላይ ማብራሪያ የሚፈልግ ተጫራች በዚህ የጨረታ ሰነድ ላይ በተመለከተው የሻጭ አድራሻ የሚፈልገውን ማብራሪያ በፅሑፍ መጠየቅ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ያለባቸው ከሻጭ ብቻ ነው፡፡ ተጫራቾቹ የጨረታ ሰነዱን በቀጥታ ከሻጭ ካለማግኘታቸው ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ማንኛውም ዓይነት ጉድለት ወይም አለመሟላት ሻጩ ተጠያቂ አይሆንም።
- ሻጭ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር
ስልክ ቁጥር 011 460 701748/ 011 470 0751