በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1. እስቴሸነሪ፣
  • ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ሎት 3. የመኪና ጎማ እና ባትሪ፣
  • ሎት 4. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 5. ናፍታ እና ቤንዚን ትራንስፖርት፣
  • ሎት 6. የመኪና የሞተር ዘይት እና የጥርሳ ጥርስ ዘይት፣
  •  ሎት 7. ጀኔሬተር፣
  • ሎት 8. ፈርኒቸር፣
  • ሎት 9. በርና መሰኮት እንዲሁም
  • ሎት 10. ዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡

፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ (ቲን) ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  3. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉበት የግብር ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በእያንዳንዱ ሎት የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) (ቢድ ቦንድ) ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ከጥቅምት 23/2019 ዓ/ም እስከ ህዳር 02/2019 ዓ/ም ድረስ በጋዜጣ ይውላል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከጥቅምት 23/2019 ዓ/ም እስከ ህዳር 02/2019 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት /ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 ህዳር 03/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  12. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ወድቅ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም እና ስምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16.  የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
  17. ተጫራቾች ከሎት 1-9 ድረስ ያሉ የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመዉ ጃናሞራ ወረዳ/መ/ብርሃን ንብረት ክፍል ሲሆን ሎት 10 ማለትም ዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ርክክብ የሚፈጸመው ማ/ጎ/ ዞን ከሻጭ መጋዝን ይሆናል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ትራንስፖርት አንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
  18.  ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ
ገንዘብ ጽ/ቤት