Addis Zemen (Nov 03, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር -14/2019
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሀዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት፤
- የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፤
- አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፤
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፤
- የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፤
- የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች፤
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች (ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ጥራቱን በጠበቀ ስካን በማድረግ ኦንላይን የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው ጊዜ መሰረት በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ኦንላይን በኦከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሀዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO ለእያንዳንዱ ኮድ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. ቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ወይም ወደ ኦክሸን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በአካል በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 7ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ8ኛው ቀን ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡ በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት (3) ቀናት የሚመለስላቸው ይሆናል።
- ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ በተለጠፈው ፎቶ ብቻ ተመልክተው ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚጭኑት/የሚያቀርቡት ሰነድ ጥራቱን በጠበቀ መሳሪያ ስካን የተደረገ እና አስፈላጊ የሆነ ሰኖዶች ብቻ እንዲያቀርብ ይመረጣል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ 09-05-11-55-11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ሥራ ሂደት የስልክ ቁጥር፡-046-212-53-96 / 046-220-1936 ይደውሉ።
የቴሌግራም ግሩፕ:- https://t.me/hawassaawegaged (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018)
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት