የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የተለያዩ አገልግሎቶች እና እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የተለያዩ አገልግሎቶች እና እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 03, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 002/2019

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች እና እቃዎች ማለትም:-

  • (ሎት1). የተለያዩ የደንብ ልብሶች
  • (ሎት2). የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና መለዋወጫዎች
  • (ሎት3) የመኪና ዕቃዎች
  • (ሎት4). የእንስሳት መድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች
  • (ሎት5). የመኪና ኪራይ አገልግሎት
  • (ሎት6). የIT ዕቃዎች የጥገና አገልግሎት
  • (ሎት7). ሦፍትዌር የማበልፀግ ሥራዎች
  • (ሎት8). የኔትዎርክ ዝርጋታ ስራዎች
  • (ሎት9). የማስታወቂያና ኤቨንት ኦርጋናይዘር ሥራ
  • (ሎት10). የተሸከርካሪዎች የጥገና አገልግሎት
  • (ሎት11). የመኪና ጎማዎች
  • (ሎት12). የቢሮ ወልል ምንጣፍና መጋረጃ
  • (ሎት13). የዶሮ እርባታ ኬጅ
  • (ሎት14). የከተማ ግብርና መገልገያ መሳሪዎች (የሽቅብታ እርሻ መሳሪያዎች፣ ሮቶዎች፣አከፋ፣ ዶማ፣ ውሃ ማጠጫ ወዘተ…) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1, በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ከገቢዎች የድጋፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ

5. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በየሎቱ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባችዋል እንዲሁም አሸናፊው ድርጅት ለአሸነፈባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ CPO ሲያሰሩ ለአቃ/ቃ/ክ/ከ/ዋና/ስ/አስፈጻሚ ፋይናንስ ቡድን ወይም Ak/K/S/C/C/Executive finance team ብለው ያሰሩ

(ሎት.1)

20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

(ሎት.2)

50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

(ሎት.3)

20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

(ሎት.4)

10,000.00 ( አስር ሺህ ብር)

(ሎት.5)

50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

(ሎት.6)

20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

(ሎት.7)

50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

(ሎት.8)

50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

(ሎት.9)

50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

(ሎት.10)

50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

(ሎት.11)

10,000.00 (አስር ሺህ ብር)

(ሎት.12)

20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

(ሎት.13)

50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

(ሎት.14)

50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

ተጫራቾች ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የሚገዙትን የእቃዎች እና አገልግሎቶች ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 9ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሙላት ያለባቸው ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል ላይ ኦርጅናል ኮፒ ላይ ኮፒ በማለት በታሸገ ኤንቨሎፕ እያንዳንዱን ሎት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ ለማስገባት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ከገዙት ሰነድ ወጪ በሌላ ሠነድ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

7. ተጫራቾች ለሎት 1፣4፣እና 12 የተጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን፣ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ለውድድር አይቀርብም

8. ጨረታው ከአስረኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

9. በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት የዕድገት ደረጃቸው አነስተኛ ታዳጊና ከዚያ በላይ ሆነው ከአደራጃቸው ተቋም በኃላፊ የተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ እና የደረጃ ዕድገት ሠርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 44 31 17 95 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡– ቃሊቲ መናኽሪያ ፊት ለፊት የሚገኘው የአስተዳደሩ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ላይ ነው።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን