የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ግብአቶችን (እንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ፣ የንብ ቀፎ ከነ ህብረ ንቡ፣ የዶሮ ማርቢያ ኬጅ እና የእንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ መኖ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ግብአቶችን (እንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ፣ የንብ ቀፎ ከነ ህብረ ንቡ፣ የዶሮ ማርቢያ ኬጅ እና የእንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ መኖ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 04, 2026)

ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የካ/ክ/ከተማ/ዋ/ስ/አ/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2019 በጀት አመት የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ግብአት ግዥ

  • ሎት 1 የ2 ወር እድሜ እንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ ግዥ CPO (50,000)
  • ሎት 2. ዘመናዊ ባለ ፍሬም /ዛንድራ/ የንብ ቀፎ ከነ ህብረ ንቡ ግዥ CPO (50,000)
  • ሎት 3. የዶሮ ማርቢያ ኬጅ ግዥ CPO (50,000)
  • ሎት 4 የእንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ መኖ ግዥ CPO (50,000)

ስለዚህ በጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ተጋብዘዋል።

1. የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት፡፡

5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ናሙና እንዲቀርብ የተጠየቁባቸውን ዕቃዎች መጫረቻ ሠነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የተጠየቀውን ወይም የሚወዳደሩበትን ናሙና ማስገባት ግዴታ አለባቸው፡፡

7. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከላይ በተገለፀው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ የየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። 

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒ መሆኑን በመግለፅ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9ኛ ፎቅ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆኑን /አለመሆኑን ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

12. ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ የውል ማስከበሪያ Cpo 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡

13. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ስልክ ቁጥር፡-011 8 67 81 75

የየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *