አርቲክራፍት ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህ የተበላሹ ፕሪፎርሞች፣ የፕላስቲክ ቦትሎች እና ክዳኖች (Damaged Packaging materials) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አርቲክራፍት ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህ የተበላሹ ፕሪፎርሞች፣ የፕላስቲክ ቦትሎች እና ክዳኖች (Damaged Packaging materials) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


2merkato.com (Nov 05, 2026)

 ቀን፡ 24/2/2019 ዓ.ም

የጨረታ መለያ ቁጥር፡ Arti/Damaged PM/001/2019

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን አርቲክራፍት ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህ ከዚህ በታች የተገለጸውን Damaged Packaging materials/የተበላሹ ፕሪፎርሞች፣ የፕላስቲክ ቦትሎች እና ክዳኖች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች እቃዉን ባለበት ቦታ በማየት የምትገዙበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በመግለፅ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን 24/02/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 29/02/2019 ዓ/ም ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የስራ ቀናት በአርቲክራፍት ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

ጨረታው በ 30/2/2019 ዓ.ም  4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡

1. የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ፡ ተጫራቾች ዋጋቸውን ማቅረብ የሚችሉት ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዞ በተዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ብቻ መሆን አለበት።

2. የታክስ ሁኔታ፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላም ሆነ የአጠቃላይ ዋጋ 15% ቫትን (15% VAT) ያካተተ መሆን አለበት።

3. የዘገዩ ጨረታዎች፡ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በ 30/2/2019 ዓ.ም  4:00 ሰዓት) በኋላ የሚመጡ ጨረታዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። በተጨማሪም ተጫራች ያስገባውን ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡

4. የክፍያ እና ዕቃ ማንሻ ጊዜ፡ የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ አለበት፤ እንዲሁም ክፍያ ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን አንስቶ ማጠናቀቅ ይኖርበታል።

5.ሕጋዊ ሰነዶች: ተወዳዳሪዎች ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው። አሸናፊው ተጫራች ውል ሲፈራረም ኦሪጂናል ንግድ ፈቃዱን ማሳየት ይኖርበታል።ተጫራቾች ፍቃዳቸው በመልሶ መጠቀም የስራ ዘርፍ (Recycling) የሆነ እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ያለው ስነድ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፣ ድርጅቱ ይህንን መስፈርት አሟልተው ለተገኙ ተጫራቾችን ብቻ የሚያወዳድር ይሆናል ፡፡

6. መብት: ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ :   አድራሻ፡– አርቲክራፍት ኢንደስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህ  ዱከም /መንደሎ/ ባጃጅ መገጣጣሚያ ፊት ለፊት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *