በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ አይነት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን (ኢቸር ካርጎ ደረቅ ጭነት እና ዶንፊንግ የጭነት ቫን) ባሉበት ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ አይነት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን (ኢቸር ካርጎ ደረቅ ጭነት እና ዶንፊንግ የጭነት ቫን) ባሉበት ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 06, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ አይነት ያገለገሉ የተሸከርካሪዎች ከታች በዝርዝር የቀረቡትን ባሉበት ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የመኪናው ዓይነት

መኪናው የተሰራበት ዘመን እ.ኤ.አ

መኪናው የተሰራበት ሀገር 

የጭነት መጠን

 

የሞተር ችሎታ (ሲሲ)

 

ተሸከርካሪው የሚገኝበት ቦታ

1

ኢቸር ካርጎ ደረቅ ጭነት 10.8 ሞዴል

2013

ህንድ

2 ሰው እና 50.2 ኩንታል

3298

 

ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ

2

ዶንፊንግ የጭነት ቫን

2015

ቻይና

1 ሰው እና 6 ኩንታል

1053

 

ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ

1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናቶች በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ በመቅረብ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሸከርካሪ የሚያስገቡትን ዋጋ መጠን 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ተሞልቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች መኪኖቹን ባሉበት ቦታ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ግማሽ ቀን በድርጅቱ የስራ ሰዓት በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የስራ ቀን እና የጨረታ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት 16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ ኢንዱስትሪ መንደር በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን አጠቃላይ ዋጋ ከፍሎ ተሸከርካሪውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የሚወረስ ይሆናል።

6. ለተሸከርካሪ የስም ማዛወሪያና ተያያዥ ሌሎች ወጭዎች እና ከቦታ ለወማንሳት የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ወጪዎች ሙሉ በሙሉ በገዥ የሚሸፈን ይሆናል።

7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0939554606/0912503275 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።

በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/ግ/ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *