የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል – test3.diretenders.com

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል


Addis Zemen (Nov 07, 2026)

የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ

ማስታወቂያ ቁጥር OFWE/GU-04/2019

ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ጅማ ቅ/ጽ/ቤት፤ ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት፤ አርሲ ቅ/ጽ/ቤት እና ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ እንዲሁም ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የ“Gravelea¸roubsta” ድብልቅ ግንድላ እና የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ፤ በተጨማሪ በነዚሁ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጅ ቅ/ጽ/ቤት፤ ፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት እና ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ እንዲሁም ባሌ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የ“Gravelea roubsta” ድብልቅ ግንድላ እና የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ፤ በተጨማሪ በነዚሁ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

1. የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TIN number” ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ጊምቢ ከተማ፤ ባሌ ቅ/ጽ/ቤት ጎባ ከተማ፤ ቦራና ጉጅ ቅ/ጽ/ቤት አዶላ ከተማ፤ ሀራርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ፤ ፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት ፊንፊኔ ከተማ፤ ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ጅማ ከተማ እና አርሲ ቅ/ጽ/ቤት ነጌሌ አርሲ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።

2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆይል።

3. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

5. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011240249 በመደወል ማጠየቅ ወይም www.oromiaforest.et  ድረ–ገፅ ማጎብኘት ይችላሉ፡፡

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *