Addis Zemen (Nov 09, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃ ዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 18/2019
በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በሀራጅ ጨረታ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ህዳር 03/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ ወይም ድህረ ገጽ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ከጵሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
በመሆኑም:-
1. በዕቃ ግልጽና ሀራጅ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት(ስካን በማድረግ) ኦንላይን የኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et ማያያዝ ይኖርበታል።
2. በተሽከርካሪ ሀራጅ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ (C.PO) ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. በጨረታው ላይ የዕቃው ወይም የተሸከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
4. ተጫራቾች የዕቃዎቹንና የተሸከርካሪውን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ህዳር 03/209 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን ኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
5. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CuSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CuSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተዉ ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
6. የዕቃና የተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች እንዲሁም ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 200,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት። ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን የሚወስን መሆኑን እንገልጻ። (ትንም ሲፒኤ በአካል ወደ ኦከሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጒት ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሸን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይበማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከውሰድ ቀን ጀምሮ |
የጨረታ የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
የእቃ ሀራጅ |
እስከ 07/03/2019 |
እስከ 08/03/2019 (ከ4፡00 ሠዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ደቂቃ መሠረት ይካሄዳል። |
|
2 |
የእቃ ሀራጅ |
እስከ 08/03/2019 |
09/03/2019 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል። |
|
|
3 |
የተሽከርካሪ ሐራጅ |
እስከ 08/03/2019 |
እስከ 09/03/2019 (ከ5፡00 ሠዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ደቂቃ መሠረት ይካሄዳል። |
8. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ሙሉ በሙሉ የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et (በኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ።
9. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ተሽከርካሪውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
11. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ክፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት አና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 05 11 55 11
አድራሻ:- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 (ኦክሽን ኢትዮጵያ)
በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ 0114708503
አድራሻ፦ ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈዜ መንገድ መንገጢያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት