2merkato.com (Nov 18, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር 133
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን አዳዲስ የኤሌክትሪክ (BYD-E2) እና ሌሎች የተለያየ ሞዴል ያላቸውን፤ በጠቅላላው 12 ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተወዳድሮ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተሽከርካሪዎች በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ተሽከርካሪዎች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ተሸከርካሪዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሠነዱ ላይ በሠሌዳ ቁጥራቸው እና በቻንሲ ቁጥራቸው አንፃር ባለው ክፍት ቦታ የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሰ.ፒ.ኦ ጋር በማያያዝ ካሽጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ/
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-36-91-91-91/09-30-79-64-13 ወይንም 09-75-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር