Addis Zemen (Nov 20, 2026)
የመጀመሪያ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ለበረንታ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰጠው ሁለት የአክስጅን ማምረቻ ማሽነሪዎች ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በካፒታል እቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውሉ መሰረት ሊከፍል ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሚሸጠው ንብረት |
የመነሻ ዋጋ
|
የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄድበት |
||||
|
የንብረት ዓይነት |
የሚገኝበት አድራሻ |
ብዛት |
ቦታ
|
ቀን
|
ሰዓት
|
||
|
1 |
የሚሰሩ ሁለት የኦክስጅን ማምረቻ ማሽኖች (50m3/hr እና 80m3 hr) የማምረት አቅም ያላቸው፤ አንድ ጀነሬተር (ከATS ጋር Prime Power 280 kw የሆነ) እንዲሁም 346 ሲሊንደሮች |
ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14
|
2 (ኦክስጅን ማሽን) 1 (ጀነሬተር)
|
33,040,292.78
|
የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ባህርዳር ዲስትሪክት ጽ/ቤት
|
ታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ/ም
|
4:00-6:00 |
የሽያጭ መመሪያ፡–
- ንብረቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ የሚገዛበትን ዋጋ 25% በባንክ ከፍያ ማዘዣ (CPO) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በዲስትሪክቱ ቅጥር ግቢ በአካል በመቅረብ መደራደር ይችላል።
- የኦክስጅን ማምረቻ ማሽኖቹ እና ጀነሬተሩ ቀድሞ ከተተከለበት ቦታ ተነቅሎ በባንኩ መጋዘን ውስጥ የተቀመጡ ናቸው።
- የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል። ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ከፍያው በገዥው ይፈጸማል።
- ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ ለሚገዙ ባሸነፉበት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ ከፍያን ጨምሮ አሸናፊው ይከፍላል።
- አሸናፊው የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ መስፈርት ካሟላ ሽያጩ በዱቤ ግዥ ይሆናል።
- አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ አጠቃሎ መክፈል አለበት። ካልከፈለ ባንኩ ሽያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሽያጩ በድጋሚ ይካሄዳል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ሽያጩን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡– 058-226-2740
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት