ፀደይ ባንክ አ.ማ. (ጎንደር ዲስትሪክት ድማዛ ቅርንጫፍ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 20 ኢንዳስትሪ መንደር ቁጥር 02 የሚገኘውን 1,500 ካ.ሜ የኢንዱስትሪ ሸድ እና ቦታ በግልፅ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል – test3.diretenders.com

ፀደይ ባንክ አ.ማ. (ጎንደር ዲስትሪክት ድማዛ ቅርንጫፍ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 20 ኢንዳስትሪ መንደር ቁጥር 02 የሚገኘውን 1,500 ካ.ሜ የኢንዱስትሪ ሸድ እና ቦታ በግልፅ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል


Addis Zemen (Nov 20, 2026)

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንከ አ.ማ. ጎንደር ዲስትሪክት ድማዛ ቅርንጫፍ ለወ/ሮ ሂሩት ታደለ ሉቃስ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን ጎንደር ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 20 ኢንዳስትሪ መንደር ቁጥር 02 የካርታ ቁጥር 10580/2008 የቦታው ስፋት 1500 ካ.ሜ የሆነ የኢንዱስትሪ ሸድ እና ቦታ ለንፅኅና እቃዎች ማምረቻ አገልግሎት የሚውል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል።

1. የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ግምቱ 20,389,056.58 (ሃያ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ ሃምስ ስድስት ብር ከ58/100 የሆነ

2. ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4ኛ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ ኢማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ብቻ ይሆናል።

4. በጨረታው የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።

5. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊው በ10 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

6. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።

7. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝውውሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጪዎች ገዢ ይሸፍናል/ይከፍላል/። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረውና የክፍያ ጊዜው ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።

8. ተጫራቾች ቤቱን/ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።

9. ጨረታው የሚካሄደው 17/04/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ጎንደር ከተማ አዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ፀደይ ባንክ ድማዛ ቅርንጫፍ ሲሳይ ጋራዥ ፊት ለፊት ይሆናል።

10.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡ ፀደይ ባንከ ድማዛ ቅርንጫፍ በስ.ቁ 09 18 07 75 45 (058 114 0846) ይደውሉ።

ፀደይ ባንክ አ.ማ.

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *