Addis Zemen (Jun 06, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ህዳር 02 ቀን 1957 ዓ.ም. የተቋቋመ ቢሆንም ማህበሩ ከ1966 ዓ.ም. ጀምሮ በንግድ ስራ ላይ አለመኖሩን ሰነዶች ያመለክታሉ፡፡ በአባላቱ ለፍርድ ቤት በቀረበ አቤቱታ ማህበሩን እንደገና ለማደራጀት ያልተቻለ በመሆኑ ሁኔታውን ለአባላቱ ቀርቦ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተደረገ መደበኛ እና አስቸኳይ የአባላት ስብሰባ በአባላቱ አብላጫ ድምጽ ማህበሩ እንዲፈርስ ተወስኗል።
በዚህም መሰረት የማህበሩ ሂሳብ የማጣራት ስራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
በሂሳብ ማጣራቱ ሂደትም ከማህበሩ ዓባላት በቀረበ ጥያቄ መሰረት የባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር ንብረት የሆነ 61 ሰው የሚጭን ፊያት N3 ዘመኑ ያለፈበት ለረጅም ዓመታት የቆመ ለመለዋወጫ አገልግሎት የሚውል አውቶቡስ በባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ ይገኛል።
በመሆንም ይህን ንብረት ባለበት ሁኔታ ማህበሩ በግልጽ ጨረት አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤
በመሆኑም ከላይ የተዘረዘረውን ንብረት ለመግዛት የሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች በሟሟላት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 በባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር ስም በተከፈው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01322240761900 ገቢ በማድረግ ኢአ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ከማህበሩ ቢሮ ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
1) ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በራሱ ወጪ ባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ በመገኘት መመልከት የሚችል።
2) በጨረታው ለመሳተፍ ብር 50000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም በማህበሩ ስም የባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር በተከፈው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01322240761900 ገቢ በማድረግ ማስያዝ የሚችል።
3) በጨረታው አሸናፊ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ | ድርጅት በ05(አምስት) ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመክፈል ንብረቱን ሙሉ በሙሉ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ በራሱ ወጪ እና ኃላፊነት ማንሳት የሚችል።
4) በጨረታ ሰነዱ መሰረት የሚገዛበትን ዋጋ እና የጨረታ ዋስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም ባንክ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ሰነድ በአንድ ላይ በማሸግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ኢ.ኢ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመገኘት ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ21 (ሃያ አንድ) ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚችል።
5) ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት ክፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከቀኑ በ06፡00 ሰዓት የሚዘጋ ይሆናል፡፡ ጨረታው በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኢ.አ. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 ይከፈታል።
6) ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 5 31 31 67 / 0911 12 72 65 (አቶ ዘሪሁን ደጀኔ) ወይንም 0911 67 99 69 (አቶ ንጉሴ) በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።
ዘመድሁን አዳነ ሰርቲፋይድ ኦዲት ድርጅት
የባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር (መጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ