የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን ለፈንድ ማጠናከሪያ እንዲሆን ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ያገኘውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ አና የቢሮ መገልገያዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን ለፈንድ ማጠናከሪያ እንዲሆን ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ያገኘውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ አና የቢሮ መገልገያዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 30, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን ለፈንድ ማጠናከሪያ እንዲሆን ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ያገኘውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ፣የኤሌክትሮኒክስ አና የቢሮ መገልገያዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኤፍ አካውንት ቁጥር 1000332121708 እየከፈሉ ከተቋሙ ግዢና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ አዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ህብረት ኢንሹራንስ ህንፃ 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) ቀናት ከጠዋቱ 230 ሰዓት ጀምሮ እስከ 1100 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ በአስረኛው ቀን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መሆኑን እናሳውቃለን።

2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሚል ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል። አሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ ከፍለው ሲመጡ ተመላሽ ይሆናል፤ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት በጨረታ አፅዳቂ መፅደቁ ወይም ውድቅ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸ በኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።

3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10 ቀናት ሆኖ 10ኛው ቀን ጨረታው 800 ሰአት ተዘግቶ በዛኑ ቀን 815 የሚከፈት ይሆናል።

4. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመግዛት ከሰነዱ ላይ ሙሉ ዝርዝሩን ያገኛሉ።

5. የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ አዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ህብረት ኢንሹራንስ ህንፃ 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 608 በመገኘት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

6. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁት ንብረቶች የሚገኙበት ቦታ CMC የተባበሩት አደባባይ አካባቢ ደርግ የሰራቸው ኮንዶሚኒየም ውስጥ እና ሜክሲኮ ጠማማ ፎቅ ቤዝመንት እና ልደታ ፍርድ ቤት ከጠዋቱ 400 እስከ 930 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-558-2437 / 011-558-2376 / 09-01-19-09-39 / 09-61-71-26 04

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስልጣን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *