አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. የተለያዩ ማሽነሪዎችን በሐራጅ አወዳድሮ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ተጫራች ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. የተለያዩ ማሽነሪዎችን በሐራጅ አወዳድሮ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ተጫራች ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 12, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

የሐራጅ መለያ ቁጥር 01/2018

አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ የተለያዩ ማሽነሪዎችን በሐራጅ አወዳድሮ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ተጫራች ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት መሳትፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ተጫራቾች ኩባንያው የተለያዩ 80 ማሽነሪዎች በሐራጅ የሚሸጥ ሲሆን የማሽኖቹን ዝርዝር ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የሐራጅ ሽያጭ ሰነድ ላይ የሚያገኙ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያም የሚወዳደሩበትን የማሽን አይነቶች ጠቅላላ የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባችኋል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ማሽኖቹን ኩባንያው በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት በአካል ተገኝተው ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው በመቅረብ ከጨረታው ቀን በፊት መጎብኘት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመካሄዱ ከጠዋቱ 4፡30 በፊት ባለው ጊዜ ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል በኩል ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል። ሐራጁ በቀን 19/1/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ ቃሊቲ በሚገኘው የኩባንያው መጋዘን የሚካሄድ የሆናል።
  4. ሐራጁ ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት በኩባንያው መጋዘን ውስጥ ይካሄዳል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 5ኛ ፎቅ ፋይናንስ አስ⁄ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ 200 ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6.  ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች የሐራጅ ጨረታው ከተካሄደበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ለኩባንያው አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  8. አሸናፊው ክፍያውን በፈጸመ በ10 ቀናት ውስጥ ማሽኖቹን ማንሳት አለበት፡፡

አድረሻ፡- ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተሻግሮ የ6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን በሚገኘው የኩባንያው ህንፃ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-2-179967 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ