Addis Zemen (Sep 12, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018
በደ/ኢ/ክ/መ/ ግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን
- በሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያ፣
- ሎት 2 የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣
- ሎት 3 የቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤
- ሎት 4 አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን፣
- ሎት 5 የእንስሳት መኖ ጥሬ ዕቃ ፣
- ሎት 6. የቅመማቅመም ዘር፣
- ሎት 7 የችግኝ ዘር ዓይነቶች፣
- ሎት 8. የጓሮ አትክልት ዘር፣
- ሎት 9 የግብርና ማዕድን ግብዓቶች
- ሎት 10 የተሽከርካሪ ጎማ፣
- ሎት 11 የሕንፃ መሣሪያዎች
- ሎት 12 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣
- ሎት 13 የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን፤
- ሎት 14 የእንስሳት መድኃኒትና ቁሳቁሶች፣
- ሎት 15. የስፖርት ዕቃዎች፣
- ሎት 16 የተማሪዎች ኪሊኒክ ቁሳቁስ
- ሎት 17 ዓመታዊ የሪፍሬሽመንት ግዥ እና
- ሎት 18. ዓመታዊ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም
ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መሰፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፣
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ፣ የተዕታ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የቲን ሰርተፍኬት/የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው እና ለተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት ከመንገድ ትራንስፖርት የታደሰ ደረጃ 3 እና ከዛ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለጨረታ ዶክመንቱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በሶዶ ግብርና ኮሌጅ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከፍተው በሚገኘው አካውንት ቁጥር 1000018208443 በማስገባት አድቫይስ በመያዝ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ግዥ/ክ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 41 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ፤ ለእያንዳንዱ ሎት 2፣ 5 እና 11 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ሆኖ ለሌሎቹ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር ከጨረታው ሰነድ ኮፒ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በሲፒኦ ምትክ በአማራጭነት የሚቀርብ የትኛውም ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤምቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቅስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው 16ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ግዥ/ከ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ሰርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን ዕቃዎች እስከ ከሌጁ ድረስ አቅረቦ ያስረክባል። ለአሸናፊው ዕቃ ኮሌጁ ቅድመ ክፍያ አይፈጽምም።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 551 3984/ 09 16 83 42 17 መደወል ይቻላል።
የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ /ወላይታ ሶዶ/