Addis Zemen (Sep 29, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገለ አንድ ኤፌሰር የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት የሆነ ሞዴሉ 2014 እና ሁለት ትሬሸሮች በትራክተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቧቸው 1200 የሆኑ ትሬሸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፦
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
1. ለጨረታው የወጣ ንብረትነቱ ኤፌሰር (FSR) የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት ሞዴል 2014 ንብረትነቱ የአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን የሆነ ተሽከርካሪ የሰሌዳ ቁጥር አአ-05-0243 የሊብሬ ቁጥር 401648 የሻንሲ ቁጥር JALK6A139E7102061 የሞተር ቁጥር 6HH1-473615 ሙሉ ሰፖንዳ ያለው ፤ (መነሻ ዋጋ 6,500,000 (ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር )እንደሆነ እንገልፃለን።
2. ሁለት ትሬሸሮች በትራከተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቧቸው 1200 የሆኑት የአንዱ መነሻ ዋጋ 650,000 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ) ሲሆን የሁለቱ ዋጋ አንድ ላይ 1,300,000 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ብር ) መሆኑን እንገልፃለን።
3. ተጫራቾች የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ሙገር አካባቢ ታደሰ አበበ ህንፃ ጀርባ ካለው ጊቢ ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራች ግለሰብ ወይም የገበሬ አባል ከሆነ የዘመኑ የናሽናል ID (ዲጂታል መታወቂያ) እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ያለው መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ፤ ድርጅት ከሆነ የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር መክፈሉን የሚገልጽ መረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ አለበት። እንዲሁም ሌሎች ተቋማት/ማህበራት ከሆኑ የተመዘገቡበትን ህጋዊ ሰርተፍኬት የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾቹ የግል ድርጅት ወይም የመንግስት ድርጅት ከሆነ የውክልና ደብዳቤ እና የናሽናል ID (ዲጂታል መታወቂያ) ማቅረብ አለበት።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለያንዳንዱ ለጨረታውን ለቀረቡት ንብረቶች 10% CPO በማቅረብ መጫረት ይችላሉ።
7. ለጨረታው ለቀረቡት ንብረቶች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10፡00 (ሰዓት) ድረስ በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ሙገር አካባቢ ታደሰ አበበ ህንፃ ጀርባ ካለው ግቢ ውስጥ ኤፌሰር የጭነት መኪናውን ማየት ይችላሉ።
8. ለጨረታው የቀረቡትን ሁለት ትሬሸሮች በአርሲ ዞን በጮሌ ወረዳ በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን መጋዘን ያለበት ግቢ ውስጥ በግልፅ ማየት ይችላሉ።
9. ተጫራቾች በሚወደደሩበት ንብረት ዓይነት የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ቴክኒካል ዶክመንትና ፈይናንሸል ዶክመንት አንድ(1) ኦርጅናል እና አንድ(1) ኮፒ በተለያዩ ፖስታ አዘጋጅተው አንድ ላይ በማሸግ ሌሎች የተጠየቁትን መስፈርቶች በመጨመር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዳማ ከተማ መብራት ሀይል ተስፋዬ ኦሎፒክ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ተዘግቶ በ5፡00 ሰዓት ላይ በዚሁ ቦታ ይከፈታል።
11. ጨረታው 11 ኛ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዳማ ከተማ መብራት ሀይል ተስፋዬ ኦሎፒክ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በዚሁ እለት በ5፡00 ሰዓት ላይ በዚሁ ቦታ ይከፈታል።
12. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በሁለተኛ ቀን የግዢና ሽያጭ ውል ተፈራርሞ በ1ዐ ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መውሰድ አለበት።
13 ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. የጨረታው አሸናፊ ከሽያጭ በኋላ ከስም ማዛወሪያ ጋር ተያይዞ ያሉትን ወጪዎች ከፍሎ ስሙን ወደ ራሱ ያዛውራል።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አድራሻው ከላይ በተገለፀው በዩኒየኑ መጋዘን በመገኘት ወይም
በስልክ ቁጥር 09 21 09 68 80/ 09 20 06 31 65/ 09 16 89 41 85 ደውለው መረዳት
የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
ኣድራሻችን፦ አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ 01ቀበሌ መሆናችንን እንገልፃለን። አርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ኅ/ሥ/ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ።
አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ