ዳሽን ባንክ አ.ማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ዳሽን ባንክ አ.ማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Fortune (Oct 18, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የተለያዩ ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ ሸያጭ

DB/052/2019

ዳሽን ባንክ አ.ማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለሁለተኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ቄራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል በመምጣት የጨረታውን መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 እስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በባንኩ መጋዘኖችና ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው።
  5. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
  6. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነከ ዳሸን ባንክ አ.ማ. ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣ ሆኖም በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ክፍያ በቶሎ ገቢ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ክፍያው በዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች በተዘጋጀ ሲፒኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 8 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በ5ኛው ቀን ማለትም ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ06፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ09:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
  8. በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ3 /ሶስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 /ሁለት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከባንኩ ጋር ውል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ካልፈረሙ ወይም ሙሉክፍያውን በተጠቀሰው ግዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  9. ተጫራቾችያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸውወጪ በማጓጓዝውል በፈረሙበ10 የሥራ ቀናት ዉስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  10. ባንኩ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
  11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-465 5552 ወይም 011-470 6065 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  12. ባንኩ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዳሸን ባንክ አ.ማ.

አዲስ አበባ

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

ADDING MACHINE

በቁጥር  

3

2

ELECTRICAL TYPEWRITER

በቁጥር

1

3

QUEUING MANAGEMENT SYSTEM

በቁጥር  

2

4

SWICH

በቁጥር

26

5

Monitor/ System unit

በቁጥር  

71

6

METAL DETECTOR

በቁጥር

60

7

Kama Small Generator

በቁጥር  

4

8

LOST AND FOUND DISPLAY BOARD

 በጥቅል

በጥቅል

9

NOTICE BOARD

በጥቅል

በጥቅል

10

WALL CLOCK

በቁጥር  

4

11

EPSON TERMAL PRINTER

በቁጥር  

35

12

TALLY PRINTER

በቁጥር  

12

13

NOTE COUNTING MACHINE FOR CASHER

በቁጥር  

15

14

NOTE COUNTING MACHINE FOR TELLER

በቁጥር  

17

15

MANAGERIAL TABLE

በጥቅል

በጥቅል

16

COMPUTER STAND TABLE

በጥቅል

በጥቅል

17

HIGH BACK SWIVEL CHAIR

በጥቅል

በጥቅል

18

STORAGE CABINET

በጥቅል

በጥቅል

19

LOW BACK SWIVEL CHAIR

በጥቅል

በጥቅል

20

GUEST CHAIR

በጥቅል

በጥቅል