የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኝውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኘው እርጥብ ሌጦ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኝውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኘው እርጥብ ሌጦ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


2merkato.com (Oct 29, 2026)

በድጋሚ የወጣ የዳልጋ ከብት ቆዳ፣ የበጎች እና ፍየሎች እርጥብ ሌጦ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኝውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኝው እርጥብ ሌጦ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-

  • በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ ለዳልጋ ከብት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሦስት የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና በወር ውስጥ ለሚገኝው የበግና ፍየል ሌጦ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ያለበት ሲሆን የዳልጋ ከብት ቆዳ ጨረታ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ለ10 ቀናት ብር 4,000,000.00 (አራት ሚሊዮን ብር) እና የበግና ፍየል ሌጦ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል፡፡
  • ጨረታው ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም፣ 8:15 ተዘግቶ በዚያው ዕለት 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት!!!


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *