Be'kur (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. እስቴሸነሪ፣
- ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት 3. የመኪና ጎማ እና ባትሪ፣
- ሎት 4. የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 5. ናፍታ እና ቤንዚን ትራንስፖርት፣
- ሎት 6. የመኪና የሞተር ዘይት እና የጥርሳ ጥርስ ዘይት፣
- ሎት 7. ጀኔሬተር፣
- ሎት 8. ፈርኒቸር፣
- ሎት 9. በርና መሰኮት እንዲሁም
- ሎት 10. ዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡
፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ (ቲን) ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉበት የግብር ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በእያንዳንዱ ሎት የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) (ቢድ ቦንድ) ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከጥቅምት 23/2019 ዓ/ም እስከ ህዳር 02/2019 ዓ/ም ድረስ በጋዜጣ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከጥቅምት 23/2019 ዓ/ም እስከ ህዳር 02/2019 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት /ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 ህዳር 03/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ወድቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም እና ስምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
- ተጫራቾች ከሎት 1-9 ድረስ ያሉ የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመዉ ጃናሞራ ወረዳ/መ/ብርሃን ንብረት ክፍል ሲሆን ሎት 10 ማለትም ዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ርክክብ የሚፈጸመው ማ/ጎ/ ዞን ከሻጭ መጋዝን ይሆናል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ትራንስፖርት አንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ
ገንዘብ ጽ/ቤት