Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ መገናኛ እና የኮምፒውተር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02-2018
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ መገናኛ እና የኮምፒውተር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 500ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም አያስፈልግም፡፡
- ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሃሴ 22/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡0o እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፤
- ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሃሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ፤
- የግልፅ ጨረታው ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል፤
- ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
- በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታከስ ቫት (15%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
- የሃራጅ ጨረታው ነሃሴ 23/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅጽ/ቤቱ ይካሄዳል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ 5 / በአምስት/ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፤
- ከላይ በተ/ቁ 1 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻለ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፤
- በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጭ ማድረግ አይችልም፤
- ለግልፅ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፤
- በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፤
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058-320-74 18/058-320–75-69 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻ – በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Disposal Sale cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Personal Care Products and Services cttx, cttx Sales, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Telecommunication Equipment cttx, cttx Textile, Disposals and Foreclosure cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx