Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት ያላቸውን እቃዎችና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ብቁ ከሆኑ ተወዳዳሪዎች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ድፍጤጣ/ ግልጽ /ጨ/01/2018ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት ያላቸውን እቃዎችና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ብቁ ከሆኑ ተወዳዳሪዎች ከታች በሎት የተዘረዘሩትን ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
- ሎት1, ጨርቃ ጨርቅ (ደንብ ልብስ)
- ሎት2. ቆዳ ጫማ ውጤቶችና ተዛማጅ
- ሎት3. የጽሕፈት መሳሪያዎች
- ሎት4. የህትመትና ተያያዥ ሥራዎች
- ሎት5. የቢሮ ፅዳት መገልገያ እቃዎች
- ሎት6. የቢሮ ቋሚ ኤሌክትሮኒከስ እና የኤሌከትሪክ እቃዎች
- ሎት7, የቢሮ ቋሚ የእንጨት ውጤቶች
- ሎት8. የመኪና ጎማ፣ ቅባቶችና የወንበር ልብስ
- ሎት9 የልብስ ስፌት አገልግሎት
- ሎት10, የመጫንና የማውረድ አገልግሎት (ጉልበት ሠራተኛ)
- ሎት11. አነስተኛ ሽፍን የጭነት መኪና አገልግሎት
- ሎት12. የቢሮ እቃ ጥገናና ሰርቪስ አገልግሎት
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቴከኒክ መመዘኛ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
1. ከሎት አንድ እስከ ሎት 9 ያሉት በዘርፉ የተሰማሩ የ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት (egp)፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት የታደሰ ግብር ከፋይነት ከሊራንስ የምስክር ወረቀት ያለው ማቅረብ የሚችል። የደንብ ልብስ ስፌት በ2017 ዓ.ም የተጻፈ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅበታል።
2. በሎት 10፣ 11 እና 12 ለአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት የማይገደዱ ሲሆን ሎት 10 የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ ፣ ሎት 11 ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ፣ ሊብሬ ኮፒ ፣ መኪናው ለመድኃኒት ጭነት አመቺ የሆነ ሽፍን፣ የነዳጅ እና ሌላ ፍጆታዎች በራሱ መሸፈን ሎት 12 የ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ያለው ማቅረብ የሚችል የደንብ ልብስ ስፌት በ2017 ዓ.ም የተጻፈ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅበታል። የሚችል።
3. ተጫራቾቸ ዘወትር በሥራ ቀናት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት ከ7፡30-1፡30 ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) ለእያንዳንዱ ሎት ከፍያ በ2ኛ ብሎክ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 901 በመፈጸም የጨረታ ሰነድ ከግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 907 መውሰድ አለባቸው። አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለሰነድ ግዥ ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስያዣ ለሚያመርቱት ግብዓት ብቻ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
4. ጨረታው ለ10 (አስር ቀን) የሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በጤና ጣቢያው 2ኛ ብሎከ 3ኛ ፎቅ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ አዳራሽ ቁጥር 803 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ባይገኙም የጨረታውን መከፈቻ የሚያስተጓጉል አይሆንም።
5. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋጋጠ CPO ወይም አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለጨረታ ማስከበሪያ ለሚያመርቱት ግብዓት ብቻ የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ ሲሆን ለሎት 1 ብር 20,000.00፣ ሎት2 ብር 10,000.00፣ ሎት3 ብር 20,000.00፣ ሎት4 ብር 15,000.00፣ ሎት 5 ብር 15,000.00 ፤ ሎት6.ብር 25,000.00፣ ሎት7 ብር 20,000.00፣ ሎት 8.ብር 5,000.00፣ ሎት 9.ብር 5,000.00፣ ለሎት 10.ብር 500.00፣ ለሎት 11 ብር 3,000.00 ብር፣ ሎት12 ብር 3,000.00 በድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ስም በማሠራት ከሚያቀርቡት ቴከኒካል መረጃ ጋር አሲዘው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
6. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎት ላይ ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስም ማህተም፣ ፊርማ በማድረግ የጨረታውን ዓይነት ሎት በግልጽ በመግለጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በሁሉም ሎቶች ላይ ዋጋ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም የእቃ specification በራስ ማስተካከል በዛ እቃ ወይም አገልግሎት ላይ ተወዳዳሪ አያደርግም።
7. ተጫራቾች የእቃ ናሙና እና በፎቶ ለተጠየቁባቸው እቃዎች ወይም አገልግሎት ናሙናውን ቀድመው ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በዝርዝር አስመዝግበው ማቅረብ አለባቸው በፎቶ ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ውል ከመግባቱ በፊት ጤና ጣቢያው በሚያዘው መሠረት አንድ የተሠራ ወይም የተዘጋጀ ናሙና በማቅረብ አስፈላጊ እየታ ተደርጎ ጥራቱ ከተረጋገጠ ውል ፈርሞ ቀሪ እቃ ማቅረብ አለበት።
8. ጤና ጣቢያው በመንግስት ግዥ መመሪያ መሠረት በጨረታ በግዥ ትዕዛዝ ላይ 20% የመጨመር እና 20% የመቀነስ መብት አለው። እንዲሁም አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀለት በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሲፒኦ በድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ስም አሠርቶ ማስያዝ አለበት።
9. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ጤ ጣቢያው አድራሻ መጋዘን አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል። ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
11. ጤ/ጣቢያው ለሚፈጽመው ግዥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ፡ ገርጂ መብራት ኃይል ሰብስቴሽን ጀርባ ኮብል ስቶን መንገድ ገባ ብሎ ስልክ 09-88-05-33-33
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ