የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2018

የኮልፌ ቀራኒዮ /ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ /ቤት 2018 በጀት አመት የሚከተሉት እቃዎችና አገልግሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች———- 16,000.00

ሎት 2. ደንብ ልብስ—10,000.00

ሎት 3. የቢሮ ማሽኖች የጥገና አገልግሎት (computer &Accessories)———– 3,000

ሎት 4. የፈርኒቸር ዕቃ ግዥ —————– 15000.00

ሎት 5. የጽዳት እቃዎች——– 1 6,000.00

ሎት 6. ዘር ግዥ ——- 3,000

ሎት 7. የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዥ—– 10,000.00

ሎት 8. የዲኮር ዕቃ ግዥ — 50,000.00

ሎት 9. የህንጻ እድሳት———- 10,000.00

ሎት 10. የህትመት ስራ———— 3,000,00

ሎት 11. የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ጥገና —3,000

ሎት 12. የመኪና ኪራይ (የትራንስፖርትና የጭነት)——— 2000.00

ሎት 13. የጉልበት አገልግሎት ———– 3000.00

ሎት 14. የድንኳን ግዥ————- 10,000.00

ሎት 15. የመስተንግዶ ግዥ———— 1000.00

ሎት 16. የሆቴል መስተንግዶ———— 4,000.00

ሎት17. የድንኳን ኪራይ———- 3000.00

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ፡

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 06 ፋይናንስ /ቤት አንደኛ ፎቅ ባለው ቢሮ በመገኘት የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ከሎት1ሎት 17 ላሉት እቃዎች ላቀረቡት ጠቅላላ የጨረታ ማስከበሪያ ሎቶች ፊት ባለው ዋጋ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት ስም CPO በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር የታሸገ እና በማህተም የተመታ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፤

4. ተጫራቾች ለአንድ እቃ አንድ ዋጋ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፤

5. ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል ማጫረት ይችላሉ፤

6. የጨረታ ሰነዱን ማቅረቢያ የመጨረሻው ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ሆኖ በ11ኛ ቀን 330 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡-400 ሰዓት ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 06 ፋይናንስ /ቤት ቢሮ ይሆናል። ሆኖም አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፤

7. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡

8. /ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃዎች ናሙና በሙሉ በየሎቱ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው፤

10. ተጫራቾች የወሰዱትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መቀየር አይችሉም፡፡

11. ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው ተቋም ሰነድ የሚወስዱበትና የውል ዋስትና ደብዳቤ ማፃፍ አለባቸው::

12.ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለባቸው፡፡

አድራሻ ቤቴል አደባባይ ዝቅ ብሎ ፖስታ ቤት ፊለፊት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት

ተጨማሪ መረጃ፡ስልክ ቁጥር 0113696984/0113697912

የኮልፌ ቀራኒዮ /ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ /ቤት