በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ የትምህርት እና የቢሮ አላቂ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃ፣ ልዩ ልዩ እቃዎች፣ የስፖርት እቃ፣ የላብራቶሪ እቃዎች፣ የተማሪ መመገቢያ ሼድ እና መኪና ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት እንዲሁም ለመከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የሚሊንየም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት 2018. ለመስሪያ ቤቱ ስራ አገልግሎት የሚውሉ፡

  • ሎት 1. የደንብ ልብስ
  • ሎት2. የትምህርት እና የቢሮ አላቂ እቃዎች
  • ሎት 3. የፅዳት እቃዎች
  • ሎት4. ቋሚ እቃ
  • ሎት5. ልዩ ልዩ እቃዎች
  • ሎት6. የስፖርት እቃ
  • ሎት 7. የላብራቶሪ እቃዎች
  • ሎት 8. የተማሪ መመገቢያ ሼድ
  • ሎት 9. መኪና ኪራይ

በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት እንዲሁም ለመከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ በዘርፉ የተሰማራቹ ህጋዊ ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድረን በጥራት እና በዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ከሆኑት ድርጅቶች ለመግዛት የምንፈልግ መሆኑን እያሳወቅን።

  • ተጫራቾች 2018 . የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)የተሰጠው፤
  • ወቅታዊ 2017 . የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  • በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት (Supplier List) ውስጥ የተመዘገቡ፤
  • በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጨረታ ተሳትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ /ቤት ቀኑ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የሚሊንየም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጠዋቱ 2:30-11:00 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የእቃዎች ዝርዝር ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ በመሙላት 2 በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰነዱን አሽገው ዋናውን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታው እስከሚያበቃበት 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከዋለ ከጠዋቱ 300 ታሽጎ በዕለቱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡(ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም)።
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የእቃ አይነት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ህጋዊ ማህተም ያረፈበት ሊሆን ይገባል።
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም።
  6. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅሬታ ተጠብቆ 8-15 ቀን ውስጥ በተወዳደሩበት ዋጋ እና በቴክኒክ አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10%/አስር ፐርሰንት CPO/ ለግዢ ፈጻሚ አካል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. በጨረታው ያሸነፈ ተጫራች ለአሸነፋቸው ዕቃዎች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት የማስጫኛና ማውረጃ ወጪ በመከፈል በሚሊንየም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  8. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች በጨረታ ለቀረቡት እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. ከጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለምታመጡ ድርጅቶች በምትወዳደሩበት ዘርፍ የራሳችሁ ምርት(አምራች) መሆናችሁን የሚገልፅ መረጃ በማቅረብ በአመረታችሁት እቃ ላይ ብቻ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን።
  11. /ቤቱ አሸናፊ ተጫራች ከመረጠ በኋላ በሚገዙት እቃዎች ብዛት እና መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% /ሃያ ፕርሰንት| የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን ብር በመመሪያው መሰረት ከታወቀ ባንክ የጨረታ ማስከበርያ CPO በት/ቤቱ ስም በማሰራት ከጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

.

የግዥ አይነት

ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ

1

የደንብ ልብስ

1

20000

2

የትምህርትና የቢሮ አላቂ እቃዎች

2

20000

3

የፅዳት እቃዎች

3

18000

4

ቋሚ እቃ

4

12000

5

ልዩ ልዩ እቃዎች

5

5000

6

የስፖርት እቃ

6

7000

7

የላብራቶሪ እቃዎች

7

10000

8

የተማሪዎች መመገቢያ ሼድ

8

15000

9

የመኪና ከራይ

9

2000

አድራሻ፦

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊንየም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት አጠና ተራ ድልድይ ስር ወደ ፍሊጶስ በሚወስደው መንገድ 20 ሜትር ገባ ብሎ ስልክ፡011-280-42-34/35

በአዲስ ከተማ ክፍ ከተማ የሚሊንየም

አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት