የአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ብረታ ብረቶች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች፣ የመኪና ዕቃዎችንና በአጠቃላይ ለምርምር ሥራ የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል 2018 የበጀት ዓመት ማዕከሉ ለሚያመርታቸው የምርምር ዕቃዎችና ቴከኖሎጂዎች ግብዓት የሚውሉ

  • ብረታ ብረቶች፣
  • የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
  • ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች፣
  • የመኪና ዕቃዎችንና በአጠቃላይ ለምርምር ሥራ የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 በመሆኑም፡

  1. ለሚጠየቁ የግዥ እቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውና በፌዴራል ወይም በክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት /ቤት የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት /Suppliers list/ ያላቸውና የተመዘገቡበትን የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration NO) እና ቲን ነምበር ዋናውን እና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው /ቤት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ሰነድ የማይመለስ 800.00 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አሰላ በሚገኘው የማዕከሉ /ቤት ድረስ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልተገኙም በሌሉበት 16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 500 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 530 ሰዓት በአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ቢሮ ቁጥር 24 ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 80,000.00 ታዋቂ በሆነ ባንክ “CPO” ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 022 331 1861/022 331 2492/09 12 263 915 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአሰላ ግብርና

ምህንድስና ምርምር ማዕከል