የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 26, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር /EEP/DS/01/17/

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፤

  • ሎት-1- መልካ ሰዲ የእንፋሎት /ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት የመጡ ከፍተኛ መጠን፣ ዓይነትና ዋጋ ያላቸው ዕቃዎችና ማሽነሪዎች፤ ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መልካ ሰዲ ከተማ በፕሮጀክት ጣቢያ ቅጥር ግቢ፤

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፤

ማሳሰቢያ፡ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡

1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሰ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ አክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት የተቋሙ ጣቢያዎች በመገኘት መመልከት ይቻላል፤

4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ ... በማሠራት ወይም ደግሞ በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ... በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

7. ጨረታው 20/12/2017 እስከ 5/13/2017 . እስከ ጠዋት 400 ድረስ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።

9. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ... ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፤

10. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ ሊሰረዝ ይችላል፤

11. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

12. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

13. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-558-14-24 ወይም 011-558-06-49 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *