Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. ለረጅም ጊዜ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ዓይነት ቲዮታ ኮሮላዎች፣ ሚትስቡሽ ላንሰሮች፣ ቼቭሎሌት፣ ጂሊ ሳባ እና ሊፋን አውቶ ሞቢሎች እንዲሁም ባለሁለት ገቢና ቢሾፍቱ እና ቲዮታ ሃይሉክስ ፒክ አፖችን በአጠቃላይ 52 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በተመጣጣኝ መነሻ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር FA-04/2025/26
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) ለረጅም ጊዜ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ዓይነት ቲዮታ ኮሮላዎች፣ ሚትስቡሽ ላንሰሮች፣ ቼቭሎሌት፣ ጂሊ ሳባ እና ሊፋን አውቶ ሞቢሎች እንዲሁም ባለሁለት ገቢና ቢሾፍቱ እና ቲዮታ ሃይሉክስ ፒክ አፖችን በአጠቃላይ 52 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በተመጣጣኝ መነሻ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተቀመጠውን መመሪያ መከተል ይጠበቅበታል።
የጨረታ መመሪያ፦
1. የንብረቶቹን ዝርዝር ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከጳጉሜ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ቅርንጫፍ ሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 የማይመለስ ብር 400 (ብር አራት መቶ) ገቢ በማድረግና የጨረታውን ሰነድ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመውሰድ እና ንብረቱ በሚገኝበት ሸገር ከተማ ሱሉልታ በሚወስደው መነአቢቹ ክ/ከተማ ሚዛንን አለፍ ብሎ በቻይና ጋራጅ ወደ ቀኝ በሚያስገባዉ ቅያስ ከዋናዉ መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ የባንኩ ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት መስከረም 06 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት እንዲሁም በመዝጊያው እለት መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ።
2. ገዥዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት እና የግብር ከፍያ ምዝገባ ሰርትፊኬት (TIN No) ቁጥር ያላቸዉ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ ራንግ ሪልስቴት ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ።
3. ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከተገለጸበት ከጳጉሜ 02 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጨረታው መዝጊያ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በዚያው ዕለት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጨረታው 8፡30 ሰዓት ላይ ቦሌ መንገድ ራንግ ሪልስቴት ሕንፃ 7ኛ ፎቅ የፋሲሊቲዎች እና ንብረት አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበትን ንብረት /ጨረታ/ መነሻ ዋጋውን 10% (ሃያ አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታው አሸናፊዎች ባሸነፉበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ የቦሎ እና ከስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ይከፍላል፤ እንዲሁም ተጨራች የሚገዛበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% የሚያካትት ወይም እንደማያካትት በግልጽ መግለጽ ይኖርበታል፤ ምንም ባይገለጽ ባንኩ የቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን አካቶ እንደቀረበ ታሳቢ ያደርጋል።
6. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ ከባንኩ ከተቀበለበት ዕለት ጀምሮ ያሸነፈበትን አጠቃላይ ዋጋ በ 5 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል የሽያጭ ውል መፈጸም አለበት ፤ በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሽያጩን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
8. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ራንግ ሪል እስቴት ህንፃ 7ኛ ፎቅ የባንኩ ንብረት አስተዳደር ቢሮ
ስልክቁጥር፡– 0115 576174 ፖ.ሳ.ቁ.16936/አዲስአበባ/
የኦሮሚያ ኀብረት ስራ ባንክ /አ.ማ/
ማህበረሰብን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ!