የጋሞ ልማት ማህበር ጋልማ/ ዋና ጽ/ቤት ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ያገለገሉ ንብረቶች ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ እስካኒያ መኪናዎች፣ ኖቬዶች፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች እና ሌሎች ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጋሞ ልማት ማህበር ጋልማ/ ዋና /ቤት በጋልማ የአርባ ምንጭ እርሻ ልማት በጋልማ የጋሮ ተሸከርካሪዎች ጥገናና መለዋወጫ እና በጋልማ የአርባ ምንጭ አዞ ራንች ቅጥር ግቢ የሚገኙና ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች እና ሌሎች ያገለገሉ ንብረቶች ለቢሮና ለመኖሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡

  1. ተጫራቾች እንደየንብረቶቹ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የማቅረብ በጥሬ ገንዘብ የማስያዝ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን በጨረታው ካሸነፉ ከሚገዙት ንብረት ላይ ታሳቢ የሚሆን ሲሆን በጨረታው ካላሸነፉ ያስያዙት ገንዘብ /ሲፒኦ/ ይመለስላቸዋል። የሚያስይዙት /CPO/ /ጥሬ ገንዘብ /በሠነድ ላይ በእቃዎች ፊት ለፊት የተገለፀው ይሆናል።
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ንብረቶች በጋልማ የአርባ ምንጭ እርሻ ልማት እና በጋልማ የጋሮ ተሽከርካሪዎች ጥገናና መለዋወጫ እና በጋልማ የአርባ ምንጭ አዞ ራንች ቅጥር ግቢ በማንኛውም የሥራ ሰዓት መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ማንሳት አለባቸው ካላነሱ ድርጅቱ ንብረቶቹ የቆዩበት 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በየቀኑ ኪራይ ያስከፍላል፣
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር ሥራ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይጨምራሉ፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 800 ሰዓት ድረስ በጋሞ ልማት ማህበር ዋና /ቤት ግዥና ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፣
  6. ጨረታው 15ኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 830 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ተጫራቹ ወኪሉ በቦታው ባይገኝም የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም።
  7. ልማት ማህበሩ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  8. ከዚህ ጨረታ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ጥያቄዎች በስልክ ቁጥር 0916482815 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
  9. የድርጅቱ አድራሻ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ነው።

የጋሞ ልማት ማህበር/ጋልማ

አርባ ምንጭ