Your cart is currently empty!
ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ንብረቶቹን መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቆርኪ ፋብሪካ ወደ ሚድሮክ ተርሚናል በሚያልፈው አስፋልት መንገድ ገብቶ አሉሙኒየም ፋብሪካ ፊት ለፊት በስተቀኝ በኩል በሚገኘው የኩባንያችን የከባድ ተሽከርካሪዎች ጊዜያዊ ማቆሚያ ስፍራ እና ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ጀርባ መድን ዲኮር አጠገብ በሚገኘው የቀላል እና መለስተኛ ተሽከርካሪዎች ጊዜያዊ ማቆሚያ ስፍራ (የኩባንያችን ሪከቨሪዎች) ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በቦታው በመገኘት እና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ደንበል ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የኢንጅነሪንግና ሪከቨሪ ሃንድሊንግ አገልግሎት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ደንበል ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የኢንጅነሪንግና ሪከቨሪ ሃንድሊንግ ቢሮ ውስጥ ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚቀርበው ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ሲሆን የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋቸው ከብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር ከ00/100) በላይ ለሆኑ ንብረቶች የሚጫረቱበትን ንብረት የመነሻ ዋጋን 10% (አስር በመቶ) እንዲሁም የጨረታ መነሻ ዋጋቸው ከብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር ከ00/100) በታች ለሆኑ ንብረቶች ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ከ00/100) በንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ስም የተዘጋጀ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ከጨረታው በፊት ዕዳዎች ቢኖሩ በኩባንያው ይሸፈናል:: በጨረታው ለተካተቱ ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።
- የጨረታ አሸናፊዎች የመክፈያ ቀናቶች ኩባንያው የጨረታ ውጤቱን ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ሲሆን አሸናፊዎች ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤቱ የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማስታወሻ፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911753503፤0913-943333 0911784339 ይደውሉ
ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)