Your cart is currently empty!
እናት ባንክ አ.ማ ያገለገሉ ቋሚ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ መለያ ቁጥር እባ/006/2018
እናት ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ያገለገሉ ቋሚ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ተ.ቁ |
የተሸከርካሪው ዓይነት |
ታርጋ ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የምርት ዘመን |
መነሻ ዋጋ |
የተጫራች መነሻ ዋጋ |
መግለጫ (ማብራሪያ) |
1 |
ቼቭሮሌት መኪና 1500 ሲሲ |
3-99431AA |
KL1TM5CY8DB123675 |
2013 |
520,000.00 |
|
ባለበት ሁኔታ |
2 |
ቼቭሮሌት መኪና 1500 ሲሲ |
3-85731AA |
KL1TM5CY3BB280110 |
2011 |
480,000.00 |
|
ባለበት ሁኔታ |
3 |
ቼቭሮሌት መኪና 1500 ሲሲ |
3-85734AA |
KL1TM5CY2BB279451 |
2011 |
480,000.00 |
|
ባለበት ሁኔታ |
4 |
ሞተር ሳይክል (YAMHA) |
3-1430AA |
MEIFE43FOD2015726 |
2012 |
30,000.00 |
|
ባለበት ሁኔታ |
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል ካሳንቺስ ከሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግዥ እና ፋሲሊቲ መምሪያ 5ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዝሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ ለማየት የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ባንኩ በሚያመቻቸው ቀን እና ሰዓት በመቅረብ ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ።
3: ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋት 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ፤ ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በመግዛት በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለፀው አድራሻ እስከ መስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው:: ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ የሚመጣ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
4. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መስከረም 23 /2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግዥ እና ፋሲሊቲ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነው።
5. ተጫራቾች መኪኖቹን በተመለከተ ለጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ወይም ለብቻው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. ተጫራቾች ሞተርሳይክልን በተመለከተ ለጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ወይም ለብቻው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት(5) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ በመክፈል ንብረቶቹን በአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
8. አሸናፊዎች ባሸነፉበት ዋጋ ላይ ለመንግስት የሚከፈል 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተ.እ.ታ ይከፍላሉ እንዲሁም በገዥ በኩል የሚከፈሉ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችን ገዥ ይከፍላል።
9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. የበለጠ መረጃ ለማግኘት በዚህ ስልክ ቁጥር ይጠቀሙ 0115 585 014
ማን እንደ እናት!