በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 12, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ 

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የእድገት ጮራ 2 ደረጃ /ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ ግዥ
  • ሎት 2 ለአላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 3 ለህትመት
  • ሎት 4 አላቂ የህክምና እቃ
  • ሎት 5 ለአላቂ የት/ እቃዎች
  • ሎት 6 አላቂ የጽዳት ዕቃ
  • ሎት 7 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 8 ቋሚ ኤሊክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት 9 ለህንፃ ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ጥገና
  • ሎት 10 የቋሚ ኤሌክትሪክ ጥገና
  • ሎት 11 አገልግሎት
  • ሎት 12 የመኪና ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳደሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርብ።

2. የገቢዎችእና ጉምረክ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት /ቫት/ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር መያያዝ የሚችሉ መሆን አለበት።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ በአንድ ሎት 100 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታ የስራ ቀናት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ዕድገት ጮራ አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ሎት 2 ሎት 5 ሎት 6 ሎት 7 ሎት 8 እነዚህ ሎቶች ለእያንዳንዳቸው 10,000 /አስር ብር እንዲሁም ሎት 3 ሎት 4 ሎት 9 ሎት 10 ሎት 11 ሎት 12 የመኪና ኪራይ እነዚህ ሎቶች ለእያንዳንዳችው 2000 ሁለት ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ብቻ ማስያዝ አለበት።

7, የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መጻፍ ይኖርበታል። የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና /specification/ ማቅረብ አለባቸውአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከታወቀ በኃላ በ15 ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል አለበት።

ተጫራቾች ያሸነፉበትን ደረጃውን የጠበቀ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ በናሙናው መሰረት አጠናቀው ለት/ቤቱ ንብረት ክፍል ሲያስረክቡና በጥራት ኮሜቴ ተፈትሾ ሲያልፍና በተቋሙ ኃላፊ ገቢ እንዲሆን ከታዘዘ በኃላ ይከፍላቸዋል።

8. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 400 የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዛው እለት 430 ሰዓት ዕድገት ጮራ 2 ደረጃ /ቤት ግንብ አሥ የቡድን መሪ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ C.P.O ብቻ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. አድራሻ፡ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ገመናዬ ማርያም / መግቢያ ላይ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ፡በስልክ ቁጥር 011 8 93 26 98/011 8 93 14 07

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ዕድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት