Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የደንብ ልብስ ግዥና ስፌት
- ሎት 2. የጽሕፈት መሣሪያዎች
- ሎት 2 ልዩ ልዩ ኅትመቶች
- ሎት 3 የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች
- ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 5 የአንቲቫይረስ ሶፍት ዌር
- ሎት 6. የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸሮች
- ሎት 7. የቢሮ መጋረጃ፣ የግድግዳ ልባስ ፓኔል፣ አልሙኒየም ፓርቲሽን ፍላይ ውድ እና መስታወት ሥራ እና የተለያዩ የበር እና የመሳቢያ ቁልፎች ሲሆኑ
በጨረታውን መሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
ሀ. ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
ለ. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/፣ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
ሐ. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚጫረተበትን ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
መ. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከመቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
ሠ. ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ የሚረቱበትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
ረ. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን መ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማኅተም፣ ፊርማ በማሳረፍ እና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ሰ. ጨረታው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3:30 ሰዓት ከታሸገ በኋላ በዕለቱ ከቀኑ በ4፡ዐዐ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም በ11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ሸ. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ቀ. ማንኛውም ተጫራች ዋጋውን በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
በ. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 558-0715 ወይም ዐ9 11 36 05 27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ከፌዴራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት ወደ ልደታ ቤ/ን በሚወስደው መንገድ ትንሽ
ከፍብሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር ፅ/ቤት