Your cart is currently empty!
የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ አይስፓክ፣ ፎም ፓክ፣ ካርቶኖች፣ ጎማዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር መአኤ/02/2017
የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ አይስፓክ፣ ፎም ፓክ፣ ካርቶኖች፣ ጎማዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በሟሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ውስጥ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ / ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎቹን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል። የዕቃዎቹ የመነሻ ዋጋ 20 በመቶ(20%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መዝናኛ ክበብ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ4 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- የመድኃነት አቅራቢ አገልግሎት ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ዕቃዎቹን በ5 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በሰልክ ቁጥር 011-2765 294 ወይም 011-2783-008 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልገሎት
cttx Disposal Sale cttx, cttx Materials cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Packaging and Labelling cttx, cttx Plastic Products cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Sales, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Vehicle and Machinery Foreclosure cttx, cttx Vehicle and Machinery Sale cttx, Disposals and Foreclosure cttx