ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በዋናው መስሪያ ቤት ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ያገለገሉ አሮጌ እና ዳግም አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው የብረት ፓኔሎች፣ የውሃ ፓምፕ፣ የግንባታ ቫይብሬተር ከአክሰሰሪ ጋር ባሉበት ሁኔታ በጅምላ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-01/2018

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በዋናው መ/ቤት ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ያገለገሉ አሮጌ እና ዳግም አገልግሎት መስጠት የሚችሉ

  • የተለያዩ መጠን ያላቸው የብረት ፓኔሎች፣ የውሃ ፓምፕ፣ የግንባታ ቫይብሬተር ከአክሰሰሪ ጋር ባሉበት ሁኔታ በጅምላ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ማንኛውም ተጫራች ንብረቶቹ ባሉበት መካኒሳ ዋናው መስሪያ ቤት በመመልከት እና የጨረታ ሰነዱን በብር 100 /አንድ መቶ ብቻ / 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 309 በመግዛት ከጥቅምት 10 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 /2018 ዓም እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለጠቅላላው ንብረቶች የጅምላ ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በመክተት መጫረት የሚቻል መሆኑን እየገለጽን ማንኛውም ተጫራች በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በኤንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት መካኒሳ ዋናው መስሪያ ቤት ይከፈታል።

ድርጅቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 09114602479 ወይም 091114852 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ