Your cart is currently empty!
የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ሲገለገልባቸው የነበሩትን ቶዮታ ተሸከርካሪዎችንና ሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቅያ
የጫረታ ማስታወቂያ ቁጥር – 01/2018 – አዲስ አበባ
የቅድስትማርያም ዩኒቨርሲቲ ሲገለገልባቸው የነበሩትን ቶዮታ ተሸከርካሪዎችንና ሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች
በቢሮው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ከጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከዩኒቨርሲቲው ሂሳብ ክፍል በመቅረብ በብር 300 (ሦስት መቶ) ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች የሚገዙትን ቶዩታ ተሸከርካሪዎች እና ሞተር ብስክሌት ሜክሲኮ ከፌደራል ፓሊስ ዋና መስሪያ ቤት ወረድ ብሎ ከኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ በስተቀኝ ገባ በሎ በሚገኝ የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ዋና ቅጥር ግቢ በመገኝት ትራንስፖርት ቢሮውን በማነጋገር ተሸከርካሪዋችን መመልከት ይቻላል።
- ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት ተሽከርካሪዋች የሚያቀርቡትን ዋጋ በጨረታ ዶክሜንቱ ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚህ ጫረታ በተዘጋጀላቸው ሳጥን ውስጥ ጨረታው እሰከ ሚዘጋበት እሰከ ጥቀምት 17 ከጠዋቱ 4:30 2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በቅድስት ማርያም ዩኒቨርስቲ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዥ (ሲፒኦ) ከጫረታ ሰነድ ጋር ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን አሽናፊው ወዲያውኑ እንዲታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት(ሲፒኦ) ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ10 ቀናት ወስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
- የጨረታ ተሳታፊዎች ወደ ጫራታው ሲመጡ ማንነታችውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዎል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ወይንም የማራዘም መብት አለው።
አድራሻ፡ ሜክሲኮ ከፊደራል ፓሊስ ወረድ ብሎ ኦሊቢያ ነዳጅ ማድያ ወደ ቀኝ ገባ በሎ
ስልክ ቁጥር፡ 0115 580 616 / 0911 241 445 / 0912 167 291 / 0930 011 003
ንግድ ባንክ አካውንት 1000173538832