Your cart is currently empty!
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ አዲስ እና ያገለገሉ የመኪና ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ጨረታ ቁጥር 006/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ አዲስ እና ያገለገሉ የመኪና ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡–
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 006/18 በ22/02/2018 የተለያዩ አዲስ እና ያገለገሉ የመኪና ዕቃዎች ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈረግ ማንኛውም ተጫራች
- በዘርፋ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥርን ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል።
- ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
- በሐራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሪሲት በመውሰድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ 12፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። ነገር ግን ዕቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ነው።
- በሐራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በሐራጅ ጨረታ ለመጫረት ዕቃዎች ለመግዛት ለሚያቀርበው ዋጋ 5% በጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል።
- በሐራጅ ጨረታ ለወጡት በእያንዳንዱ ኮዶች በጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO የዕቃውን ዋጋ 5% ብር በባንክ (ንግድ ባንክ የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል።
- የሐራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታውቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒአ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ዕቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ከፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተሜራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲሞን ለባለስልጣኑ መቤት ገቢ ሆኖ ዕቃ በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- የጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70(09 12 88 57 46) መደወል ይቻላል።
ጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት