Your cart is currently empty!
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለተለያዩ አገልግሎቶች ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር Disposal 0008/2018
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለተለያዩ አገልግሎቶች ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. በጨረታ የሚሳተፍ ድርጅት ከሆነ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
2. ተጫራቾች አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በሚገኘው ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 4 በአካል ተርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ስም ብቻ በዳሸን ባንክ የሂሳብ ቁጥር 0001001218018 በማስገባት ያስገቡበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለጨረታ ያቀረበበትን 10% የጨረታ ማስከበሪያ በMOHA SOFT DRINKS INDUSTRY SC. CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የሚፈልጉትን የተሽከርካሪ ዓይነትና የሠሌዳ ቁጥር ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ እንዲሁም ከሲ.ፒ.ኦ ጋር በማካተት የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛው የስራ ቀን ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ድረስ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 4 ለመረጡት ተሽከርካሪ ፋይናንሽያል ፕሮፖዛላቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።ጨረታው በዕለቱ ከጠዋት 4፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡45 ይከፈታል።
5. ተጫራቾች አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በሚገኘው ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ተሽከርካሪዎቹን ማየት ይችላሉ!
6. ድርጅቱ ማንኛውንም የመንግስት ዕዳ ከፍሎ ተሽከርካሪዎቹን ለመሸጥ የሚያስፈልግ ክሊራንስ በራሱ ወጪ ከሚመለከተው የመንግሥት መ/ቤት ያቀርባል፡፡
7. የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዟቸው ተሽከርካሪዎች የስም ማዛወሪያ እና በመንገድ ትራንስፖርት ግምትና የሽያጭ ውል ልዩነት ካለ ለአገር ውስጥ ገቢ የሚከፈል ወጪ በተጫራቾች ይሸፈናል፡፡
8. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ /ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ6 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ተሽከርካሪ ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን ማንሳት ሲኖርበት ተሽከርካሪውን ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO እንዲወረስ ይደረጋል፡፡
9. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ስነድ CPO ለተጫራች እንዲመለስ ይደረጋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ ሕጋዊ መብት አለው፡፡
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ
ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 4
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251911998813/ +251911663804/ +251989751653 ይጠቀሙ።
ማሳሳቢያ፡-
ተጫራቾች ሙሉ አድራሻ እና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ