የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ህትመት፣ የህንፃ መሳሪያዎችና ብረታብረት፣ የከባድ ተሸከርካሪ መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የዕህል ወፍጮ፣ ፊኖ ዱቄት አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Be’kur(Oct 27, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 ህትመት፣ ሎት 5 የህንፃ መሳሪያዎችና ብረታብረት ሎት 6 የከባድ ተሸከርካሪ መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት 7 በኤሌክትሪክ የሚሰራ የዕህል ወፍጮ ሎት 8 ፊኖ ዱቄት አቅርቦቶችን በግልጽ  ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረበረ የሚችሉ፡፡

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

6. የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ  መግዛት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ጠቅላላ ድምር ውጤት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ አንድ በመቶ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡

9. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅ ፖስታዎች ማለትም፡- ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጥቅምት 17/2018 እስከ ህዳር 01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሆነ ባይገኙም በሰዓቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ህዳር 02/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

12. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በሞባይል ቁጥር 09 18 73 44 61 /09 64 79 28 60  በመደወል  መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ