Your cart is currently empty!
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባህርዛፍ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በሰ/ሸዋ ዞን ባሶና ወረና ወረዳ ጉዩ በረት ቀበሌ ዱቤ ሸገር የመንግስት ደን ውስጥ የሚገኘውን ሁከት ከፍልፋይ 7167.50 ሜ/ኩብ ፣ቀርሳ የመንግስት ደን ውስጥ ብዛቱ 521.92 ሜ/ ኩብ አና ድንኳን የመንግስት ደን ውስጥ ብዛቱ 427.98 ሜ/ኩብ በድምሩ 8117.40 ሜ/ኩብ የነጭ ባህርዛፍ ቁም ደን እና በምዕ/ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ወረዳ ቀረር የመንግስት ደን ውስጥ 14 ክፍልፋይ የምርት መጠኑ 3791.159 ሜ/ኩብ ቀይ ባህርዛፍ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች:
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተአታ /VAT/ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ከጨረታ የቀረበውን ቁም ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይትላሉ።
5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን በኦርጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ‹‹ቁም ደን የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ›› ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሸጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታ።
7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተአታን አይጨምርም። ሆኖም አሸናፊው ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተአታን ጨምሮ ይከፍላል።
8. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
9. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 058 226 3095፣ ደ/ታቦር 058 441 0306፣ ደ/ብርሃን 011 637 5017፣ እንጅባራ 058 227 0485፣ ደ/ማርቆስ 058 871 9004፣ ኮ/ቻ 09 14 71 66 36 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባህር ዳር