የተለያዩ ንብረቶች ሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Yedebub Nigat(Feb 07, 2026)

የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በአፈም ከሳሽ አቶ ዘላለም ለገሰ እና በአፈ/ም ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ይስሃቅ መካከል ስላለው የአፈም ክስ ክርክር ጉዳይ በሀዋሳ ከተማ አዲስ ክ/ከተማ ፊላደልፊያ ቀበሌ ውስጥ በአፈ/ም ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ስም የሚታወቀው ተ/ቁጥር 1- 10 ድረስ ያለው ንብረት ዝርዝር እና የዋጋ ግምት ሆኖ በሀራጅ እንዲሸጥ እና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ በቀን 02/6/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/6/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ የሀራጅ ሽያጭ በቀን 17/6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ እንዲሸጥ ተወስኗል

ስለሆነም ፡-

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች ለጨረታው ማስከበሪያ መነሻ ዋጋውን 1/4 በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 030 በአካል ቀርባችሁ በማስያዝ እና ያስያዛችሁበትን ህጋዊ ደረሰኝ ይዛችሁ በመቅረብ ጨረታውን መሳተፍ ትችላላችሁ

በጨረታው ለተሸነፈ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያ ይመለስለታል

ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ  ይኖርበታል

ያሸነበፈትን የጨረታ ገንዘብ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ካላደረገ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ማስታወቂያ ወጥቶ ጨረታ ይካሄድበታል

ጨረታውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ይፈጸምለታል

የጨረታው ሂደት የሚካሄደው በ17/6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ከተማ አዲስ ክ/ከተማ በፊላደልፊያ ቀበሌ ውስጥ በአፈ/ም ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ይስሃቅ ስም በሚታወቀው ግቢ ውስጥ እንደ ሆነ አውቀው በተባለው ጊዜ ውስጥ እንድትገኙ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

.

የዕቃ ዝርዝር

የአንዱ ዋጋ

ጠቅላላ ዋጋ

1

ፕላስቲክ ወንበር

500*42

21,000.00

2

ባለጌ ወንበር

500*3

1,500.00

3

ጮራ ፕላስቲክ ጠረጴዛ

650*14

9,100.00

4

ሳምሰንግ ቲቪ 42 ኢንች

19,000.00

19,000.00

5

ብርጭቆ

35*32

1,120.00

6

የቢራ ሳጥን

300*24

7,200.00

7

ፍሪጅ ዲፕ(መካከለኛ)

1500*1

15,000.00

8

ፍሪጅ ዲፕ(Accer ትልቁ

35,000*1

35,000.00

9

ፍሪጅ የቁም

7,000*1

7,000.00

10

የድራፍት ማሽን

38,000*1

38,000.00

 

ጠቅላላ ድምር 153,920( አንድ መቶ ሀምሳ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ብር)

 

 

በሲዳማ/ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት