Your cart is currently empty!
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላ ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ድንጋይ፣ አሸዋ፣ ቆርቆሮ፣ እንጨት፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ጠጠር፣ ሚስማር፣ አጠቃላይ የግንባታ እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላ ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ድንጋይ ፤አሸዋ ፤ ቆርቆሮ ፤ እንጨት ፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ፤ ጠጠር ፤ ሚስማር ፤ አጠቃላይ የግንባታ እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የግብር መላያ ቁጥር ወይም ቲን ነምበር ያላቸው
4. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት / ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው
6. የሚገዙ የእቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ተጫራቾቹ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ተዕዛዝ ወይም ( ሲ.ፒ.ኦ ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ በም/ወ/ወ/የሳላ ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ማስገባት ይኖርበታል። ጨረታው በወጣበት በ15ኛው ቀን ከ11፡30 ላይ ይዘጋል።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በም/ወ/ወ በሰላ ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ተጫራቹ ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም የማሽን አይነቶች በአንድ ላይ የሚያቀርብ መሆን አለበት።
12. ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0116 250 497 ወይም 0921 127 777 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ይህ ማስታወቂያ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና በአላት የሚውል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀናት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
በአብክመ ከተማ መሠረተ ልማት ቢሮ በሰ/ሸዋ ዞን መስተዳደር የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላ ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት